Services

What We do

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

1. የሒሳብ ስራ

ሓምሌ 1 ስላለፈው አመት ግብር ለማሰብ በጣም የዘገየ ጊዜ ነው። ለዚህም ነው በአለማየሁ ሀብቴ አካውንቲንግ አገልግሎት ከፍተኛ ገቢ ላላቸው የግብር ከፋዮች እና የአነስተኛ ቢዝነሶች የሒሳብ እና የምክር አገልግሎት ጭምር በመስጠት አስቀድመን የግብር አከፋፈል ስትራቴጂ በመንደፍ በተቻለ ፍጥነት አና በጥራት ሒሳቡ በጊዜ እንዲዘረጋ የምናደርገው። እንደ አጠቃላይ የታክስ እቅድ ሂደታችን አካል፣ ማንኛውም የንግድ ወይም የቢዝነስ መዋቅር በተቻለ መጠን ውጤታማና የተስተካከለ መሆኑን እናረጋግጣለን። የንብረት ግዢ ወይም ሽያጭ  ታክስን እና ክፍያዎችን በተመለክት የንግደዎን ጥቅሞች ያስጠበቀ፣ ጤናማ እና አድሮ ችግር ያማስከትል እንዲሆ ከመሰረቱ እናማክርዎታለን እንረዳዎታለን። እንዲሁም ለወደፊቱ የግብር ስትራቴጂዎ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የግብር ህግ ለውጦችን በጊዜ እንዲያውቁ እናግዝዎታለን።

2. ሒሳብ መዝጋትና ታክስ ማሳወቅ

3. ቫት በየጊዜው ማሳወቅ (Vat Declaration)

የተጨማሪ እሴት ታክስ መግለጫ (Tax Declaratio) ማለት አንድ ታክስ ከፋይ ምን ያህል ተ.እ.ታ መክፈል እንዳለበት ወይም ምን ያህል ተ.እ.ታ መከፈል እንዳለበት ለታክስ አስተዳደር በተወሰን የጊዜ ገደብ (በወር ወይም በሩብ ዓመት) ያከናወናቸውን ተግባራት ጠቅለል አድርጎ የሚያሳውቅበት ሰነድ ነው። ከአላስፈላጊ ቅጣት ለመዳንና በጊዜ እዳውን አውቆ ትርፍና ኪሳራ ለማወቅ በተወሰነለት ጊዜ ከስህተት የጠራ ስራ ወቅቱን ጠብቀን የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያዎን እናሳውቅሎታለን።

4. ዋጋ ማውጣት

ዋጋ ማውጣት የTax Optimization ዘዴ አንዱ አካል ነው። ይህም ማለት በሚፈቀደው የትርፍ ህዳግ ውስጥ እንዴት አድርገው ውጤታማነትዎን ያረጋግጣሉ ነው። ይህ አሰራር የረጅም ጊዜ ልምድና ብልሃት የሚጠይቅ ተገቢ ቀመር እና ስሌት የሚያስፈልገው በመሆኑ እኛ ጋር ቢመጡ ውጤታማ ይሆኑበታል።

5. የቢዝነስ የአማካሪነት አገልግሎት (Busiess Consultancy)

ከንግዱ ባህሪ፣ ከውስጥ ሂደት ተግዳሮቶች፣ ከወጪና ገቢ ማመጣጠን ችግሮች፣ የገበያ መፈለጊያና መፍጠሪያ መንገዶች ካለማወቅ ጋር በተያያዘ ችግር ቢገጥምዎ ወይም አዲስ የንግድ ስራ ስትራቴጂ ቢፈልጉ፣ ያሰቡትን የወደፊት ስኬትዎን ለማንፀባረቅ ልናማክርዎ ከጎንዎ ነን።

የእኛ የንግድ አማካሪዎች ከዛሬው የገበያ ተለዋዋጭነት ጋር እንዲላመዱ እና እርስዎ ሊያጋጥሙዎት የሚችሉ አደጋዎች ምንም ቢሆኑም መወዳደርዎን እንዲቀጥሉ ሊረዱዎት ይችላሉ። ዲጂታል ማርኬቲንግን ጨምሮ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንዴት ቢዝነስዎን ማስፋት እንደሚችሉ እናግዝዎታለን።

6. በደምበኛ ጥያቄ መሰረት የገበያ ጥናት ማካሄድ (Market Research)

ገበያዎን ማስፋት ወይም አዲስ ገበያ ሰብረው መግባት ሲፈልጉ የገበያ ጥናት በማካሄድ እናግዞታለን

7. የገበያ የአማካሪነት አገልግሎት (Marketing Consultancy)

ከንግድዎ፣ ባጀትዎ እና የእድገት እቅድዎ ጋር የሚጣጣሙ የተለያዩ የግብይት ምክር አገልግሎቶችን እንሰጣለን። ሁሉም የንግድ ድርጅቶች የተለያዩ ፍላጎቶች እንዳላቸው እንገነዘባለን። ስለዚህም እያንዳንዱን ደንበኛ በተናጠል ፍላጎቱን በማጥናት አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ብቻ እናቀርባለን። ሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤታማ እና ወጥነት ያለው የግብይት ስትራቴጂ በመቅረጽ የሚከወኑ ናቸው።

የቢዝነስ ግንኙነት (Business Relations Consultancy)

በባለሙያዎች የታገዘ የገበያና የንግድ ግንኙነት የማማከር ስራ ለመጀመር ያነሳሳን በቴክኖሎጂ ውስጥ ብዙ አዳዲስ ፈጠራዎች እየተከሰቱ ቢሆንም፣ የሚለካ የንግድ ሥራ ውጤቶችን ለማግኘት ጥቂት ኩባንያዎች ብቻ የግብይት ፈጠራቸውን ለመጠቀም የቻሉት በመሆናቸው ነው። ባለሙያዎቻችንና አጋሮቻችን በአንድነት ለድርጅት ፈጣን ተቀባይነትና ጥሩ ስም በሚያመጣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ  ልምድ በዛሬው የዲጂታል አለም የግብይት መስፈርት መሰረት ያደረግ ዝግጅት አድርጓል። በዚህ መሰረትም ለደንበኞቻችን ስትራቴጂክ የግብይትና የንግድ ግንኙነት በሃገር ውስጥና በውጭ ባሉ ገበያዎች ውጤታማ ለመሆን ይሚያስችል የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን::

ድርጀትዎን ኮምፒዩተራይዝ ማድረድ (Business Computerization)

ስራዎን ለማቀላጠፍ ድርጅትዎን ኮምፒተራይዝ ማድረግ ሲፈልጉ እኛን ያማክሩን

10. ለድርጅትዎ ድረ-ገጽ መስራት (Website Design and Development)

ድረ-ገጽ የሌለው ድርጅት ሰዎች ኢንተርነት ውስጥ ፈልገው ስለማያግኙት ተደራሽነቱ ደካማ ይሆናል። ስለዚህ ወደኛ ይምጡና ድር-ገጽ ያሰሩ።

ለድርጅትዎ ሶፍትዌር መስራት (Software & Application Development)

ድርጅትዎ ዘመናዊ የICT ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ አስበው ከሆነ ለApplication Development እኛ ጋር ይምጡ።

Free Estimation

For your Requests

Use our Email Addresses