አለማየሁ ሃብቴ የሒሳብ አገልግሎት ድርጅት

About Us

አለማየሁ ሃብቴ የሒሳብ አገልግሎት

አለማየሁ ሀብቴ የሒሳብ አገልግሎት በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ኩባንያዎች አጠቃላይ የሂሳብ አገልግሎቶችን የሚሰጥ እውቅ ተቋም ነው። ከአጠቃላይ የሂሳብ አያያዝ እና የግብር ተመላሾች እስከ የፋይናንስ ትንበያ እንዲሁም የቢዝነስ አማካሪነትን ጨምሮ ሰፊ አገልገሎቶችን ይሰጣል። ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ልምድ ያለን የሒሳብ ሥራ ድርጅት እንደመሆናችን፣ ደንበኞቻችንን ትርፋማ ለማድረግ እና በሒሳብ አያያዝ ጉድለት ከሚመጡ አደጋዎች ለመጠበቅ ጥንቃቄ ያልተለየው ስራ እንሰራለን። የደንበኞቻችን የቢዝነስ ሚስጥሮችን ለመጠበቅም የቢዝነስ ዲሲፕሊን መርህዎችን በጥንቃቄ እንተገብራለን። ይህም ከሩብ ክፍለዘመን በላይ አብረውን የዘለቁ ደንበኞቻችን የሚመሰክሩት እውነት በመሆኑ ከፍተኛ  ኩራት ይሰማናል። የእኛ ብቸኛ አላማ የእርስዎን ቢዝነስ ወቅታዊ እና ቀጣይ  ውጤታማነት ማረጋገጥ ነው።

የሒሳብ ስራ

ከኛ ጋር ከሆኑ ከግብር ጋር በተያያዘ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ስጋቶች ተላቀው በልበሙሉነት ስራዎትን መስራት ይችላሉ። የእኛ ባለሙያዎች በየጊዜው የሚለዋወጠውን የገቢ ግብር ኮድ እና አሰራር በአንክሮ በመከታትል በጊዜ በበቂ ጥንቃቄ ስለእርስዎ ስራውን ይሰራሉ።   

ስትራቴጂክ የታክስ እቅድ ማውጣት፣ ህጋዊ ጉዳዮችን በጊዜ ማሰተካከል። ችግሮች ሲያጋጥሙ በእርስዎ ቦታ ሆነን የመከራከርና የማስተካከል ስራም እንሰራለን። ከሁሉ በላይ ግን ችግሮች እንዳይከሰቱ ሂሳቦን በጥንቃቄ እንሰራለን።

የታክስ መጠንና ሁኔታዎች አስቀድመን ለእርስዎ በማሳወቅም በቂ ዝግጅት እንዲኖርዎት እናደርጋለን።

As Featured In:

Free Estimation

በንግድ ስራዎ የሚያሳስቦት ነገር ካለ እኛ ጋ ይምጡ

ወደኛ በቀረቡ ቁጥር ለጥያቄዎቸዎ መልስ ያግኛሉ!